FANDOM


ምዕራፍ፡ ፲።Edit

፩፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ በሌሊቱ፡ ማግስት፡ ንስር፡ ከባሕር፡ ሲወጣ፡ በሕልም፡ አየሁ፡ (መንግሥተ፡ ባቢሎን፡) ክንፎችም፡ አሥራ፡ ሁለት፡ ናቸው፡ ራሶቹም፡ ሦስት፡ ናቸው።

፪፤ በክንፉም፡ በዓለሙ፡ ሁሉ፡ ይበራል፡ (በሥልጣኑ፡ ዓለሙን፡ ሁሉ፡ ይገዛል፡) የሰማይ፡ ነፋሳትም፡ ሁሉ፡ ይነፍሱበታል፡ (መኳንንት፡) ደመናትም፡ በሱ፡ ይሰበሰባሉ።

፫፤ ከነዚያም፡ ክንፎቹ፡ ራሶች፡ ይበቅላሉ፡ (ልጆች፡ ይወልዳሉ፡) እነዚያም፡ ራሶች፡ ታናናሽ፡ ክንፍ ይሆናሉ፡ ደካሞች፡ ይሆናሉ።

፬፤ ራሶቹም፡ ዝም፡ ይላሉ፡ ከነዚያም፡ ራሶቹ፡ የመካከለኛው፡ ራሱ፡ ይበልጣል፡ ነገር፡ ግን፡ እሱም፡ ከነሳቸው፡ ጋራ፡ ዝም፡ ይላል።

፭፤ ያም፡ ንሥር፡ ምድርን፡ ይገዛት፡ ዘንድ፡ በምድር፡ ያሉ፡ ሰዎችንም፡ ይገዛቸው፡ ዘንድ።

፮፤ ከሰማይ፡ በታች፡ ያሉ፡ ሁሉ፡ ይገዙለት፡ ዘንድ፡ በክንፉ፡ ይበራል፡ ያንንም፡ ንስር፡ በዚህ፡ ዓለም፡ ከተፈጠረው፡ ፍጥረት፡ የሚከራከረው፡ የለም።

፯፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ያ፡ ንሥር፡ ተነሥቶ፡ በጥፍሮቹ፡ ቆሞ፡ ቃሉንም፡ አሰምቶ፡ ጮኸ።

፰፤ ክንፎቹንም፡ ሁላችሁ፡ ከናንተ፡ አንዱም፡ አንዱም፡ በየቦታችሁ፡ ተኙ፡ እንጂ፡ ሁላችሁ፡ አንድነት፡ አትነሡ፡ በየጊዜው፡ ትነሣላችሁ።

፱፤ የኋለኛይቱ፡ ራሱ፡ ከሁሉ፡ ትበልጣለች፡ አለኝ፡ (ከፋርስ፡ በኋላ፡ የተነሣች፡ መንግሥት፡ ጽርዕ፡ ከሁሉ፡ ትበልጣለች)።

፲፤ ባየሁ፡ ጊዜ፡ የሚገዙ፡ ከዘመዶቹ፡ የሚወለደው፡ ነው፡ እንጂ፡ ከሱ፡ የሚወለደው፡ አይደለም።

፲፩፤ የነዚያ፡ የራሶች፡ ቊጥርም፡ ስምንት፡ ናቸው፡ (የሊህ፡ የነገሥታት፡ ቊጥርም፡ ስምንት፡ ናቸው)።

፲፪፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ በቀኝ፡ በኲል፡ ወጣ፡ ዓለሙንም፡ ሁሉ፡ ገዛ፡ አለ። (ከዚህ፡ በኋላ፡ በባቢሎን፡ ቀኝ፡ ያለ፡ መንግሥተ፡ ሜዶን፡ ተነሣ፡ ዓለሙንም፡ ሁሉ፡ ገዛ፡)

፲፫፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ጥፋቱ፡ በደረሰ፡ ጊዜ፡ ቦታው፡ የማይታይ፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ እሱም፡ ጠፋ፡ አለ፡ ሁለተኛውም፡ ወጣ፡ እሱም፡ ብዙ፡ ዘመን፡ አጽንቶ፡ ገዛ፡ አለ፡ (ባልንጀራው፡ ፋርስ፡ ተነሣ፡ ብዙ፡ ቀንም፡ አጽንቶ፡ ገዛ፡)

፲፬፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ የሚጠፋበት፡ ቀን፡ በደረሰ፡ ጊዜ፡ እሱም፡ እንደ፡ ፊተኛው፡ ጠፋ።

፲፭፤ ቃል፡ መጣለት።

፲፮፤ ምድርን፡ ይኸን፡ ያህል፡ ዘመን፡ አጽንተህ፡ የገዛሃት፡ አንተ፡ አሞራ፡ ሳትጠፋ፡ ይኸን፡ የምነግርህን፡ ስማ፡ አለ፡ (ዓቢይ፡ አንጥያኮስ፡)

፲፯፤ ካንተ፡ በኋላ፡ እንዳንተ፡ የሚጸና፡ የኩሌታህንም፡ እኩሌታ፡ እንዳንተ፡ የሚገዛ፡ የለም፡ (አፊፋኖስ፡)

፲፰፤ ሦስተኛውም፡ ወጣ፡ እሱም፡ ከሱ፡ አስቀድሞ፡ እንደ፡ ነበረው፡ አጽንቶ፡ ገዛ፡ ከዚህ፡ በኋላ፡ እሱም፡ ጠፋ።

፲፱፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ዳግመኛ፡ ክንፎቹ፡ (ነገሥታቱ፡) ሁሉ፡ ወጡ፡ እያንዳንዳቸውም፡ ገዙ፡ ዳግመኛ፡ ሁሉም፡ ጠፉ።

፳፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ አጽንተው፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ በግራ፡ በኩል፡ በየጊዜያቸው፡ ክንፎቹ፡ (ነገሥታቱ፡) ተነሡ፡ ነገር፡ ግን፡ ፈጥነው፡ ጠፉ።

፳፩፤ ከሳቸውም፡ የተነሡ፡ አሉ፡ ነገር፡ እነሱ፡ አልገዙም።

፳፪፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ እሊህ፡ አሥራ፡ ሁለቱ፡ ክንፎቹ፡ (ነገሥታቱ፡) ጠፉ፡ እሊህም፡ ሁለቱ፡ ራሶቹ፡ (ነገሥታቱ፡) ጠፉ።

፳፫፤ ዝም፡ ከሚሉ፡ ከሦስቱ፡ ራሶቹ፡ (ነገሥታቱ፡) በቀር፡ ከዚህ፡ አሞራ፡ ወገን፡ የቀረ፡ የለም፡ ከስድስቱ፡ (ነገስታቱ፡) ራሶቹም፡ በቀር፡ የቀረ፡ የለም።

፳፬፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ከሊህ፡ ከስድስቱ፡ ራሶቹ፡ ሁለቱ፡ ተለይተው፡ ሄዱ፡ በቀኝ፡ በኩል፡ ባለ፡ ራሱ፡ ውስጥ፡ የተቀመጡ፡ አራቱ፡ ግን፡ በቦታቸው፡ ቀሩ።

፳፭፤ እሊህ፡ አራቱ፡ ራሶች፡ (ነገሥታቱ፡) ግን፡ ይቆሙ፡ ዘንድ፡ አለሱም፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ ተማከሩ።

፳፮፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ አንዱ፡ ተነሥቶ፡ ቆመ፡ ነገር፡ ግን፡ ፈጥኖ፡ ጠፋ።

፳፯፤ ሁለተኛውም፡ እንደሱ፡ ከፊተኛው፡ ይልቅ፡ እሱ፡ ፈጥኖ፡ ጠፋ።

፳፰፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ከሞት፡ የቀሩት፡ እሊህ፡ ሁለቱ፡ ነግሠው፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ እንደሱ፡ ተማከሩ።

፳፱፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ እሊህም፡ ሲማከሩ፡ ዝም፡ የሚሉ፡ ከሦስቱ ራሶች፡ መካከለኛ፡ የሚሆን፡ አንዱ፡ ተነሣ፡ ከነሳቸው፡ የሚበልጥ፡ እሱ፡ ነው።

፴፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ እሊህን፡ ሁለቱን፡ ራሶች፡ ከሱ፡ ጋራ፡ ወሰዳቸው።

፴፩፤ ያም፡ ራስ፡ አብረውት፡ ካሉ፡ ጋራ፡ ተመለሰ፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ የተማረኩ፡ እሊህን፡ ሁለቱን፡ ራሶች፡ ዋጣቸው፡ ድል፡ ነሣቸው።

፴፪፤ ያም፡ ራስ፡ (አፊፋኖስ፡ አንጥያኮስ፡) አጽንቶ፡ ገዛ፡ በሷም፡ የሚኖሩ፡ ሰዎችን፡ በብዙ፡ ድክም፡ መከራ፡ አጸናባቸው፡ ከቆሙት፡ ከሊህ፡ ክንፎች፡ ሁሉ፡ ይልቅ፡ ፈጽሞ፡ ዓለምን፡ ቀማ።

፴፫፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ መካከልለኛው፡ ራስ፡ እንደ፡ እለዚያ፡ ጠፋ፡ (አፊፋኖስ።)

፴፬፤ ሁለቱ፡ ራሶች፡ ቀሩ፡ (አጀም፡ ሮም፡) እነሱም፡ እንደነሱ፡ ምድርን፡ ገዟት፡ በውስጧ፡ ያሉትንም፡ ገዟቸው።

፴፭፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ይህ፡ በቀኝ፡ እኩል፡ ያለው፡ ራስ፡ (በጥሊሞስ፡) በግራ፡ እኩል፡ ያለውን፡ ዋጣው፡ (አንጥያኮስ፡)

፴፮፤ በፊትህ፡ ተመልከት፡ የምታየውንም፡ እወቅ፡ ያለኝን፡ ቃል፡ ሰማሁ።

፴፯፤ ባየሁም፡ ጊዜ፡ እየጮኸ፡ እነሆ፡ ከምድረ፡ በዳ፡ አንበሳ፡ ተነሣ፡ እንደ፡ ሰውም፡ ሲናገር፡ ሰማሁት፡ ያንም፡ አሞራ።

፴፰፤ የምነግርህን፡ እግዚአብሔርም፡ ያለህን፡ አንተ፡ ስማ።

፴፱፤ ምድርን፡ ይገዟት፡ ዘንድ፡ ከፈጠርኋቸው፡ የዘመንም፡ ፍጻሜ፡ ከሚደርስባቸው፡ ከሊህ፡ ካራት፡ እንስሳ፡ (ነገሥታት፡) የቀረህ፡ አንተ፡ አይደለህምን፡ ያለህን፡ ስማ።

፵፤ አራተኛውም፡ መጥቶ፡ ያለፉትን፡ በብዙ፡ ድካም፡ በብዙ፡ ሕማም፡ ይህ፡ ዓለም፡ የቀሙትን፡ እለዚያን፡ እንስሳ፡ ሁሉ፡ ድል፡ ያደርጋቸዋል፡ ያለህ፡ አንተ፡ ስማ፡ ይህን፡ ያህል፡ ዘመን፡ በዚህ፡ ዓለም፡ በተንኰል፡ ኖሮ።

፵፩፤ ይችን፡ ዓለም፡ በጽኑ፡ አገዛዝ፡ ገዛት፡ ያለህ፡ አንተ፡ ስማ።

፵፪፤ ጻድቃንን፡ ቀምተሃቸዋልና፡ ደጋጎቹ፡ ሰዎችንም፡ በድለሃቸዋልና፡ ቅኖቹንም፡ ጠልተህ፡ አሰተኞቹን፡ ወደሃቸዋልና፡ የጻድቃንን፡ አምባቸውን፡ አፍርሰሃልና፡ ያልበደሉትን፡ ሰዎች፡ ቅጽራቸውን፡ አፍርሰሃልና።

፵፫፤ ኃጢአትህም፡ ወደ፡ እግዚአብሔር፡ ደርሳለችና፡ ትቢትህም፡ ወደ፡ ኃያል፡ እግዚአብሔር፡ ደርሷልና።

፵፬፤ እግዚአብሔርም፡ ወገኖቹ፡ መቃብያንን፡ በቸርነቱ፡ ተመልክታችኋልና፡ መቃብያን፡ መከራ፡ የሚቀበሉት፡ ዘመን፡ እነሆ፡ ተፈጽሟልና።

፵፭፤ ስለዚህ፡ ነገር፡ አንተ፡ አፊፋኖስ፡ አንጥያኮስ፡ ትጠፋለህ፡ ኃጢአተኞች፡ ወገኖችህ፡ የእግዚአብሔርን፡ ሕግ፡ የዘነጉ፡ ጥቃቅን፡ ነገሥታቶችህም፡ ክፉዎች፡ የሆኑ፡ ሠራዊቶችህም፡ ይጠፋሉ።

፵፮፤ ምድርም፡ ከመከራዋ፡ ሁሉ፡ እፎይ፡ ብላ፡ ካንተ፡ ታርፍ፡ ዘንድ፡ የፈጣሪዋን፡ ቸርነቱንና፡ ፍርዱን፡ ተስፋ፡ ያደርግ፡ ዘንድ፡ በደለኞች፡ ዘመዶችህም፡ ይጠፋሉ።