FANDOM


ምዕራፍ፡ ፲፩።Edit

፩፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ፈጣሪ፡ እግዚአብሔር፡ ለዚያ፡ ላሞራ፡ ይህን፡ ቃል፡ በነገረው።

፪፤ የቀረው፡ ይህ፡ ራስ፡ ጠፋ፡ (አፊፋኖስ፡ ጠፋ፡) ወደሱ፡ የመጡ፡ እነዚያም፡ ክንፎች፡ (ነገሥታት) ተነሡ፡ እሊህም፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ ተነሡ፡ በጥፍራቸውም፡ (ሠራዊት፡) ይታወካሉ።

፫፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ እነሱም፡ ጠፉ፡ ሥጋቸውም፡ ሁሉ፡ ተቃጠለ፡ ምድርም፡ ፈጽማ፡ ደነገጠች፡ እኔም፡ ከብዙ፡ ምርምር፡ የተነሣ፡ ደነገጥሁ፡ በጽኑ፡ ፍርሃትም፡ ነቃሁ።

፬፤ ልቡናዬን፡ የእግዚአብሔርን፡ ሥራ፡ ስትመረምሪ፡ አንቺ፡ ይኸን፡ ሁሉ፡ አደረግሽኝ፡ አልኋት፡፡

፭፤ ሰውነቴ፡ ደከመች፡ ልቡናዬም፡ እጅግ፡ ተጨነቀች፡ በብዙ፡ ፍራት፡ ተይዤ፡ ምንምን፡ ኃይል፡ የለኝ፡ በዚችም፡ ሌሊት፡ ደነገጥሁ።

፮፤ ለዘላለሙ፡ ያጸናኝ፡ ዘንድ፡ አሁንም፡ ወደ፡ እግዚአብሔር፡ እለምናለሁ።

፯፤ አቤቱ፡ ጌታዬ፡ በፊትህ፡ ባለሟልነትን፡ ካገኘሁ፡ ባንተ፡ ዘንድ፡ ራሴንም፡ ካስደነቅሁ፡ ልመናዬም፡ በፊትህ፡ ከደረሰች።

፰፤ ከመፍራት፡ አድነህ፡ አጽናኝ፡ አልሁት፡ ልቡናዬ፡ ፈጽማ፡ ደስ፡ ይላት፡ ዘንድ፡ የሚያስፈራ፡ የዚህን፡ የሕልም፡ ትርጓሜ፡ ለኔ፡ ለባሪያህ፡ ንገረኝ፡ አልሁ።

፱፤ በኋላ፡ ዘመን፡ የሚደረገውን፡ ስለ፡ ዓለሙ፡ ወራት፡ ኅልፈትም፡ ያሳየኸኝ፡ አንተ፡ ደግ፡ ሰው፡ አድርገሃልና፡ ና፡ የሕልምህን፡ ትርጓሜ፡ ንገረኝ፡ አልሁ።

፲፤ ያየኸው፡ የዚህ፡ የሕልምህ፡ ትርጓሜ፡ እንዲህ፡ ነው፡ አለኝ።

፲፩፤ ከባሕር፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አሞራ፡ ለወንድምህ፡ ለዳንኤል፡ በሕልም፡ የታየችው፡ አራተኛዋ፡ መንግሥት፡ (እስክንድር፡) ናት።

፲፪፤ ዛሬ፡ ላንተ፡ እኔ፡ እንደተረጐምኩልህ፡ ነገር፡ ግን፡ ለሱ፡ አልተረጐምሁለትም።

፲፫፤ እነሆ፡ ዘመን፡ ይመጣል፡ በዚህ፡ ዓለምም፡ ከሷ፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ መንግሥታት፡ ይልቅ፡ የምታስፈራ፡ መንግሥት፡ ትነሣለች።

፲፬፤ በሷም፡ አሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ ይነሣሉ።

፲፭፤ ዳግመኛ፡ የሚነግሠውም፡ ካሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ በዘመኑ፡ ፈጽሞ፡ የሚጸና፡ ነው።

፲፮፤ ያየሃቸው፡ የሊህ፡ ያሥራ፡ ሁለቱ፡ ክንፎች፡ ትርጓሜ፡ ይህ፡ ነው።

፲፯፤ ቃልን፡ ሲናገር፡ ያየው፡ ይህም፡ ከዘመዱ፡ የተወለደ፡ ነው፡ እንጂ፡ በመንግሥት፡ ሁለተኛው፡ የሚሆን፡ ከሱ፡ የተወለደ፡ አይደለም።

፲፰፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው፡ ከዚያም፡ መንግሥት፡ አፊፋኖስ፡ አንጥያኮስ፡ ይወለዳል፡ መንግሥት፡ እጠፋ፡ እጠፋ፡ ትላለች፡ በግዛቷ፡ እጅግ፡ ጸንታ፡ ትኖራለች፡ እንጂ፡ ነገር፡ ግን፡ ያን፡ ጊዜ፡ አትጠፋም።

፲፱፤ ከክንፎቹ፡ ራሶች፡ ሲወጡ፡ ያየኸውም፡ ይህ።

፳፤ ትርጓሜው፡ እንደዚህ፡ ነው፡ ዘመናቸው፡ የከፋ፡ ወራታቸው፡ ያጠረ፡ ፰፡ ነገሥታት፡ በሷ፡ ይነግሣሉ፡ ሁለቱ፡ ግን፡ ከነሳቸው፡ በዘመናቸው፡ መካከል፡ ፈጥነው፡ ይጠፋሉ።

፳፩፤ ነገር፡ ግን፡ ዓራቱ፡ መንግሥታት፡ የሚጠፉበት፡ ጊዜ፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ይጠበቃል፡ ሁለቱ፡ ነገሥታትም፡ (አጀም፡ ሮም፡) ለብዙ፡ ዘመን፡ ይጠበቃሉ።

፳፪፤ ዝም፡ ብለው፡ ያየሀቸው፡ እነዚህም፡ ሦስቱ፡ ራሶች።

፳፫፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው፡ እግዚአብሔር፡ ብኋላ፡ ዘመን፡ ሦስቱን፡ ነገሥታት፡ ያስነሣል፡ በውስጧም፡ እንግዳ፡ ነገር፡ ይሠራሉ፡ ምድርንም፡ መከራ፡ ነገር፡ ያጸኑባታል።

፳፬፤ ከሳቸው፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ ከነገሥታቱ፡ ሁሉ፡ ይልቅ፡ በውስጧ፡ የሚኖሩትንም፡ ስዎች፡ በብዙ፡ ፍራት፡ መከራ፡ ያጸኑባቸዋል።

፳፭፤ የመንግሥት፡ መገኛ፡ ናቸውና፡ ስለዚህ፡ ነገር፡ ከነገሥታት፡ በላይ፡ ተባሉ።

፳፮፤ በመኝታው፡ የሚሞት፡ ከለሳቸው፡ አንዱ፡ እሱ፡ ብቻ፡ ነውና፡ ታላቅ፡ ራሱ፡ ሲጠፋ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አንዱ፡ አንጥያኮስ፡ ነው፡ ነገር፡ ግን፡ ተጨንቆ፡ ይሞታል።

፳፯፤ የቀሩት፡ እሊህ፡ ሁለቱ፡ ግን፡ በጦር፡ ይሞታሉ።

፳፰፤ አንዱ፡ በጥሊሞስ፡ ኋላ፡ በጦር፡ ይሞታል።

፳፱፤ በየማናዊ፡ ሥልጣን፡ ወደጸና፡ ወደ፡ በጥሊሞስ፡ ሲሔዱ፡ ያየሀቸው፡ እሊህ፡ ሁለቱ፡ (አጀም፡ ሮም፡) ናቸው።

፴፤ ትርጓሜው፡ ይህ፡ ነው፡ እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቃቸው፡ የጥፋት፡ መጀመሪያ፡ የሚደረግባቸው፡ አጀም፡ ሮም፡ ናቸው፡ አንተ፡ እንዳየኸውም፡ ብዙ፡ ጸብ፡ ክርክር፡ ይደረጋል።

፴፩፤ ከምድረ፡ በዳ፡ እያናፋ፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አንበሳ፡ ያን፡ አሞራ፡ የተናገረው፡ በኃጢአቱም፡ የሰደበው፡ የሰማህ፡ ይህ፡ ሁሉ፡ ነገር።

፴፪፤ እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቀው፡ ከዳዊትም፡ ወገን፡ የሚወለድ፡ ይህ፡ አንበሳ፡ (ከደቂቀ፡ ከስሙናይን፡ አንዱም፡ አንዱ፡ ነው፡) መጥቶም፡ ኃጢአታቸውን፡ ይነግራቸዋል፡ ስለበደላቸውም፡ ይሰድባቸዋል፡ በፊታችውም፡ ፍዳቸውን፡ ይገልጥባቸዋል።

፴፫፤ በደኅነኛቸው፡ አስቀድሞ፡ ያቆማቸዋል፡ ከሰደባቸውም፡ በኋላ፡ ያን፡ ጊዜ፡ ያጠፋቸዋል።

፴፬፤ ከክህደት፡ የቀሩ፡ መቃብያንን፡ ግን፡ በቸርነቱ፡ በከበረ፡ አውራጃየ፡ (ኢየሩሳሌም፡) ያድናቸዋል፡ አስቀድሜ፡ የነገርኩህ፡ ዕለተ፡ ምጽአትም፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ደስ፡ ያሰኛቸዋል።

፴፭፤ ያየኸው፡ ይህ፡ ሕልምህ፡ እንደዚህ፡ ነው፡ ትርጓሜውም፡ እንደዚህ፡ ነው።

፴፮፤ ይህን፡ ምሥጢር፡ ታውቀው፡ ዘንድ፡ እግዚአብሔር፡ ላንተ፡ ብቻ፡ እንድታውቀው፡ አደረገህ።

፴፯፤ ነገር፡ ግን፡ ይህን፡ ያየኸውን፡ ሁሉ፡ በብራና፡ ጻፈው፡ በተሠወረ፡ ቦታም፡ አኑረው።

፴፰፤ ይህን፡ ምሥጢር፡ በልቡናቸው፡ ለመጠበቅ፡ እንዲቻላቸው፡ አንተ፡ ለምታውቃቸው፡ ላዋቆች፡ ሰዎች፡ አስተምራቸው። ...