FANDOM


ምዕራፍ፡ ፲፩።Edit

፩፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ ፈጣሪ፡ እግዚአብሔር፡ ለዚያ፡ ላሞራ፡ ይህን፡ ቃል፡ በነገረው።

፪፤ የቀረው፡ ይህ፡ ራስ፡ ጠፋ፡ [የቀረው ዘርፍ፡ ጠፋ]። ወደሱ፡ የመጡ፡ እነዚያም፡ ክንፎች፡ ተነሡ። እሊህም፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ ተነሡ፡ [ወደዚያ ዘርፍ ሔደው የነበሩት መጨረሻ ሁለት ደካም ወራሾች አሁን ግዛታቸውን ያጽናሉ]። በጥፍራቸውም፡ (ሠራዊት፡) ታወኩ።

፫፤ ከዚህ፡ በኋላ፡ እነሱም፡ ጠፉ። የንስርም፡ ሥጋ፡ ሁሉ፡ ተቃጠለ። ምድርም፡ ፈጽማ፡ ደነገጠች።

[...]

፲፤ ያየኸው፡ የዚህ፡ የሕልምህ፡ ትርጓሜ፡ እንዲህ፡ ነው፡ አለኝ።

፲፩፤ ከባሕር፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አሞራ፡ ለወንድምህ፡ ለዳንኤል፡ በሕልም፡ የታየችው፡ አራተኛዋ፡ መንግሥት፡ ናት። [በዳንኤል ምዕ. 7]

፲፪፤ ዛሬ፡ ላንተ፡ እኔ፡ እንደተረጐምኩልህ፡ ነገር፡ ግን፡ ለሱ፡ አልተረጐምሁለትም።

፲፫፤ እነሆ፡ ዘመን፡ ይመጣል። በዚህ፡ ዓለምም፡ ከሷ፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ መንግሥታት፡ ይልቅ፡ የምታስፈራ፡ መንግሥት፡ ትነሣለች።

፲፬፤ በሷም፡ አሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ ይነሣሉ።

፲፭፤ ዳግመኛ፡ የሚነግሠውም፡ ካሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ በዘመኑ፡ ፈጽሞ፡ የሚበልጥ፡ ነው።

፲፮፤ ያየሃቸው፡ የሊህ፡ ያሥራ፡ ሁለቱ፡ ክንፎች፡ ትርጓሜ፡ ይህ፡ ነው።

፲፯፤ ቃልን፡ ከሰውነቱ፡ መካከል፡ እንጂ፡ ከራሶቹ፡ ሳይሆን፡ ሲናገር፡ ያየኸው፡ ይህም፤

፲፰፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው። ከዚያም፡ መንግሥት፡ ታላቅ፡ ትግሎች፡ ይነሣሉ። መንግሥት፡ እጠፋ፡ እጠፋ፡ ትላለች። በግዛቷ፡ እጅግ፡ ጸንታ፡ ትኖራለች፡ እንጂ፡ ነገር፡ ግን፡ ያን፡ ጊዜ፡ አትጠፋም።

፲፱፤ ከክንፎቹ፡ ስምንት፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ ሲወጡ፡ ያየኸውም፡ ይህ፤

፳፤ ትርጓሜው፡ እንደዚህ፡ ነው። ዘመናቸው፡ የከፋ፡ ወራታቸው፡ ያጠረ፡ ፰፡ ነገሥታት፡ በሷ፡ ይነግሣሉ። ሁለቱ፡ ግን፡ ከነሳቸው፡ በዘመናቸው፡ መካከል፡ ፈጥነው፡ ይጠፋሉ።

፳፩፤ ነገር፡ ግን፡ ዓራቱ፡ ፍጻሜው፡ ዘመን፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ይጠበቃሉ። ሁለቱም፡ [ዙፋኑን አልፈው ወደ ሦስተኛው ዘርፍ የሚሔዱት መጨረሻ 2 ደካም ወራሾች] ለፍጻሜው፡ ዘመን፡ ይጠበቃሉ።

፳፪፤ ዝም፡ ብለው፡ ያየሀቸው፡ እነዚህም፡ ሦስቱ፡ ራሶች፤

፳፫፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው። እግዚአብሔር፡ ብኋላ፡ ዘመን፡ ሦስቱን፡ ነገሥታት፡ ያስነሣል። በውስጧም፡ እንግዳ፡ ነገር፡ ይሠራሉ፡ ምድርንም፡ መከራ፡ ነገር፡ ያጸኑባታል።

፳፬፤ ከሳቸው፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ ከነገሥታቱ፡ ሁሉ፡ ይልቅ፡ በውስጧ፡ የሚኖሩትንም፡ ስዎች፡ በብዙ፡ ፍራት፡ መከራ፡ ያጸኑባቸዋል።

፳፭፤ የመንግሥት፡ መገኛ፡ ናቸውና፡ ስለዚህ፡ ነገር፡ ከነገሥታት፡ በላይ፡ ተባሉ። [ሦስቱ የመንግሥት ዘርፎችና በመጨረሻ ብሔራዊ ጦርነት ውስጥ መሪዎቻቸው ናቸው]

፳፮፤ ታላቅ፡ ራሱ፡ ሲጠፋ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ በመኝታው፡ የሚሞት፡ ከለሳቸው፡ አንዱ፡ ነው፡ ነገር፡ ግን፡ ተጨንቆ፡ ይሞታል። [«ፊተ ጨካኝ ንጉሥ»]

፳፯፤ የቀሩት፡ ሁለቱ፡ ግን፡ በጦር፡ ይሞታሉ።

፳፰፤ አንዱ ባልንጀራውን በጦር፡ ያጠፋልና ነገር ግን እሱ ደግሞ ኋላ በጦር ይሞታል። [በ'ቀኝ' ዘርፍና በ'ግራ' ዘርፍ መካከል ያለው ብሔራዊ ጦርነት]

፳፱፤ በየማናዊ፡ ሥልጣን፡ የጸኑ፡ በቀኝ በኩል ወዳለው ራስ፡ ሲሔዱ፡ ያየሀቸው፡ እሊህስ፡ ሁለቱ፡ ታናናሽ ክንፎች [መጨረሻ ሁለቱ ደካም ወራሾች]፤

፴፤ ትርጓሜው፡ ይህ፡ ነው። እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቃቸው፡ የጥፋት፡ መጀመሪያ፡ የሚደረግባቸው፡ ናቸው። አንተ፡ እንዳየኸውም፡ ብዙ፡ ጸብ፡ ክርክር፡ ይደረጋል።

፴፩፤ ከምድረ፡ በዳ፡ እያናፋ፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አንበሳ፡ ያን፡ አሞራ፡ የተናገረው፡ በኃጢአቱም፡ የሰደበው፡ የሰማህ፡ ይህ፡ ሁሉ፡ ነገር፤

፴፪፤ እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቀው፡ ከዳዊትም፡ ወገን፡ የሚወለድ፡ መሢህ ነው [እያንዳንዱም ጊዜ ከደቂቀ፡ ሰሎሞን፡ ይወለዳል]። መጥቶም፡ ኃጢአታቸውን፡ ይነግራቸዋል። ስለበደላቸውም፡ ይሰድባቸዋል። በፊታችውም፡ ፍዳቸውን፡ ይገልጥባቸዋል።

፴፫፤ በደኅነኛቸው፡ አስቀድሞ፡ ያቆማቸዋል፡ ከሰደባቸውም፡ በኋላ፡ ያን፡ ጊዜ፡ ያጠፋቸዋል።

፴፬፤ የቀሩ፡ ወገኖች፡ ግን፡ በቸርነቱ፡ በከበረ፡ አውራጃየ፡ ኢየሩሳሌም፡ ያድናቸዋል። አስቀድሜ፡ የነገርኩህ፡ ዕለተ፡ ምጽአትም፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ደስ፡ ያሰኛቸዋል።

...