FANDOM


ከዚህ፡ በኋላ፡ በሌሊቱ፡ ማግስት፡ ንስር፡ ከባሕር፡ ሲወጣ፡ በሕልም፡ አየሁ። ክንፎችም፡ አሥራ፡ ሁለት፡ ነበሩ። ራሶቹም፡ ሦስት፡ ነበሩ።

በክንፉም፡ በዓለሙ፡ ሁሉ፡ በረረ፡ (በሥልጣኑ፡ ዓለሙን፡ ሁሉ፡ ይገዛል።) የሰማይ፡ ነፋሳትም፡ ሁሉ፡ ነፈሱበት። ደመናትም፡ በሱ፡ ተሰበሰቡ።

ከነዚያም፡ ክንፎቹ፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ በቀሉ። እነዚያም፡ ደካሞች፡ ክንፎች፡ ነበሩ። [ታናናሽ ክንፎቹ በፍጻሜ ዘመን የሚኖሩ ደካም ወራሾች ይሆናሉ።]

ሁለቱ፡ ራሶችም፡ ዝም፡ አሉ፡፡ ከነዚያም፡ ራሶቹ፡ የመካከለኛው፡ ራሱ፡ በለጠ፡፡ ነገር፡ ግን፡ እሱም፡ ከነሳቸው፡ ጋራ፡ ዝም፡ አለ። [3ቱ ራሶች ሦስት የመንግሥት ዘርፎች ናቸው፡፡]

ያም፡ ንሥር፡ ምድርን፡ ይገዛት፡ ዘንድ፡ በምድር፡ ያሉ፡ ሰዎችንም፡ ይገዛቸው፡ ዘንድ፡ ከሰማይ፡ በታች፡ ያሉ፡ ሁሉ፡ ይገዙለት፡ ዘንድ፡ በክንፉ፡ በረረ። ያንንም፡ ንስር፡ በዚህ፡ ዓለም፡ ከተፈጠረው፡ ፍጥረት፡ የሚከራከረው፡ አልነበረም። ከዚህ፡ በኋላ፡ ያ፡ ንሥር፡ ተነሥቶ፡ በጥፍሮቹ፡ ቆሞ፡ ቃሉንም፡ አሰምቶ፡ ጮኸ። ክንፎቹንም፡- «ሁላችሁ፡ ከናንተ፡ አንዱም፡ አንዱም፡ በየቦታችሁ፡ ተኙ፡ እንጂ፡ ሁላችሁ፡ አንድነት፡ አትነሡ። በየፈንታው፡ ትነሣላችሁ። የኋለኛይቱ፡ ራሱ፡ ከሁሉ፡ አለ። ባየሁ፡ ጊዜ፡ የተናገረ፡ ከሰውነቱ፡ መካከል፡ ነው፡ እንጂ፡ ከራሶቹ፡ አልነበረም። የነዚያ፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ ቊጥርም፡ ስምንት፡ ናቸው፡ [የሊህ፡ ደካም፡ ወራሾች፡ ቊጥርም፡ ስምንት፡ ናቸው]።

ከዚህ፡ በኋላ፡ መጀመርያው፡ ክንፉ፡ በቀኝ፡ በኲል፡ ወጣ። ዓለሙንም፡ ሁሉ፡ ገዛ [ከ12ቱ ታላቅ ክንፎች መጀመርያው ነው።]

ከዚህ፡ በኋላ፡ ፍጻሜው፡ በደረሰ፡ ጊዜ፡ ቦታው፡ የማይታይ፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ እሱም፡ ተሠወረ። ሁለተኛውም፡ ወጣ። እሱም፡ ብዙ፡ ዘመን፡ አጽንቶ፡ ገዛ።

ከዚህም፡ በኋላ፡ የሚጠፋበት፡ ቀን፡ በደረሰ፡ ጊዜ፡ እሱም፡ እንደ፡ ፊተኛው፡ ተሠወረ። ቃል፡ መጣለት። «ምድርን፡ ይኸን፡ ያህል፡ ዘመን፡ አጽንተህ፡ የገዛሃት፡ አንተ፡ አሞራ፡ ክንፍ፡ ሳትጠፋ፡ ይኸን፡ የምነግርህን፡ ስማ፡» አለ። «ካንተ፡ በኋላ፡ እንዳንተ፡ ረጅም፡ ዘመን፡ የሚጸና፡ የተቀበልከውንም፡ ዘመኖች፡ እኩሌታ፡ የሚበልጥ፡ አይሆንም።»

ሦስተኛውም፡ ክንፍ ወጣ። እሱም፡ ከሱ፡ አስቀድሞ፡ እንደ፡ ነበሩት፡ አጽንቶ፡ ገዛ። ከዚህ፡ በኋላ፡ እሱም፡ ተሠወረ።

ከዚህ፡ በኋላ፡ ዳግመኛ፡ ክንፎቹ፡ ሁሉ፡ ወጡ። እያንዳንዳቸውም፡ ገዙ፡ ዳግመኛ፡ ሁሉም፡ ተሠወሩ። [የቀሩት ሊገዙ ከሚገባቸው ዘመን ይልቅ ከነሱ መኃል 2ኛው ረጅም ዘመን የገዛላቸው መሪዎችን የሚመለክቱ 12ቱ ታላላቅ ክንፎች ናቸው።]

ከዚህ፡ በኋላ፡ አጽንተው፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ በቀኝ፡ በኩል፡ በየጊዜያቸው፡ የተከተሉት፡ ታናናሽ፡ ክንፎቹ፡ ተነሡ። ነገር፡ ግን፡ ፈጥነው፡ ጠፉ። ከተነሡም፡ አንዳንድ፡ ምንምን፡ ነገር፡ አልገዙም፡ [ከነዚህ 8ቱ ወራሾች መካከል አንዳንዱ ምክትል ነው እንጂ መቸም ርእሰ ብሔር አይሆንም]። አሥራ፡ ሁለቱ፡ ክንፎቹ፡ [መጀመርያ የተነሡ 12ቱ ርእሰ ብሄሮች] ሁለቱም፡ ታናናሽ፡ ክንፎቹም፡ [የሚከተለው ርእሰ ብሔርና ምክትሉ እሱም ደግሞ የዳኔል ምዕ. 8 የፍየሉ ታላቅ ቀንድ ነው] በተሠወሩበት፡ ጊዜ፡ ዝም፡ ከሚሉ፡ ከሦስቱ፡ ራሶቹ፡ [የመንግሥት ዘርፎች] ከስድስቱም፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ [ደካም ወራሾች] በቀር፡ ከዚህ፡ አሞራ፡ ወገን፡ የቀረ፡ አልነበረም።

ከዚህ፡ በኋላ፡ ከሊህ፡ ከስድስቱ፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ ሁለቱ፡ ተለይተው፡ በቀኝ፡ በኩል፡ ባለ፡ ራሱ፡ ውስጥ፡ ሄዱ፡ [የሚከተሉት 2 ወራሾች ለጊዜው ዙፋኑን አሳልፈው ከሌሎቹ መንግሥት ዘርፎች በአንዱ ውስጥ ይቆያሉ]። የቀሩ፡ አራቱ፡ ግን፡ በቦታቸው፡ ተቀመጡ [የዳንኤል ምዕ. 8 4ቱ ቀንዶች ናቸው]። እሊህ፡ አራቱ፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ [ደካም ወራሾች] ግን፡ ቆመው፡ አለሱ፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ ተማከሩ። [በዳንኤል ምዕ. 8 «እንቆቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ»ና ትዕቢተኛ ትንሹ የፍየል ቀንድ የሆነው እንዳይገዛ ተማከሩ።] ከዚህ፡ በኋላ፡ አንዱ፡ ተነሥቶ፡ ቆመ። ነገር፡ ግን፡ ፈጥኖ፡ ጠፋ።

ሁለተኛውም፡ እንደሱ፡ ከፊተኛው፡ ይልቅ፡ እሱ፡ ፈጥኖ፡ ጠፋ።

ከዚህ፡ በኋላ፡ ከሞት፡ የቀሩት፡ እሊህ፡ ሁለቱ፡ ነግሠው፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ እንደሱ፡ ተማከሩ።

ከዚህ፡ በኋላ፡ እሊህም፡ ሲማከሩ፡ ዝም፡ የሚሉ፡ ከሦስቱ፡ ራሶች፡ መካከለኛ፡ የሚሆን፡ አንዱ፡ ተነሣ። ከሌሎቹ፡ ሁለት፡ ራሶች፡ የሚበልጥ፡ እሱ፡ ነው፡ [ከሦስቱ ዘርፎች ከአንዱ ዘርፍ «ፊተ ጨካኝ ንጉስ» ይነሣል]።

ከዚህ፡ በኋላ፡ እሊህን፡ ሁለቱን፡ ራሶች፡ ከሱ፡ ጋራ፡ ወሰዳቸው፡ [«ፊተ ጨካኝ ንጉሥ» ከሌሎቹ ሁለት ዘርፎች ድገፋ ያገኛል]። ያም፡ ራስ፡ አብረውት፡ ካሉ፡ ጋራ፡ ተመለሰ። ይገዙ፡ ዘንድ፡ የተማረኩ፡ እሊህን፡ ሁለቱን፡ ራሶች፡ ዋጣቸው። ድል፡ ነሣቸው፡ [ከአራቱ ደካም ወራሾች ከመጨረሻ ሁለት ዙፋኑን ይነጥቃል]።

ያም፡ ራስ፡ [ፊተ ጨካኝ፡ ንጉሥ] ምድርን፡ ሁሉ፡ አጽንቶ፡ ገዛ። በሷም፡ የሚኖሩ፡ ሰዎችን፡ በብዙ፡ ደካም፡ መከራ፡ አጸናባቸው። ከቀደሙት፡ ከሊህ፡ ክንፎች፡ ሁሉ፡ ይልቅ፡ ፈጽሞ፡ ዓለምን፡ ቀማ፡ [በዳንኤል ምዕ. 11 ዘንድ አፍሪካን (ምጽራይም ፉጥ ኩሽ) የሚገዛ በፍጻሜም በእስራኤል ላይ የሚዞር እንዲሁም በ፪ ተስ. ዘንድ በቤተ መቅደስ ውስጥ እራሱን የሚያስቀመጥ ነው ደግሞ ራእይ 13 ያዩ]።

ከዚህ፡ በኋላ፡ መካከለኛው፡ ራስ፡ እንደ፡ እለዚያ፡ ክንፎች፡ ጠፋ። ሁለቱ፡ ራሶች፡ ቀሩ፡ [የቀሩ ሁለት መንግሥት ዘርፎች]። እነሱም፡ እንደነሱ፡ ምድርን፡ ገዟት። በውስጧ፡ ያሉትንም፡ ገዟቸው። ከዚህ፡ በኋላ፡ ይህ፡ በቀኝ፡ እኩል፡ ያለው፡ ራስ፡ በግራ፡ እኩል፡ ያለውን፡ ዋጣው፡ [አንዱ ዘርፍ ወደ ቀኝ ሲያዘንብል ሌላውንም ወደ ግራ ያለውን ድል በማድረግ የሆነ አጭር፡ ብሔራዊ ጦርነት]።

«በፊትህ፡ ተመልከት፡ የምታየውንም፡ እወቅ፡» ያለኝን፡ ቃል፡ ሰማሁ። ባየሁም፡ ጊዜ፡ እየጮኸ፡ እነሆ፡ ከምድረ፡ በዳ፡ አንበሳ፡ ተነሣ። እንደ፡ ሰውም፡ ሲናገር፡ ሰማሁት። ያንም፡ አሞራ:- «የምነግርህን፡ እግዚአብሔርም፡ ያለህን፡ አንተ፡ ስማ። <<ምድርን፡ ይገዟት፡ ዘንድ፡ ከፈጠርኋቸው፡ የዘመንም፡ ፍጻሜ፡ ከሚደርስባቸው፡ ከሊህ፡ ካራት፡ እንስሳ፡ የቀረህ፡ አንተ፡ አይደለህምን፡>> ያለህን፡ ስማ፡ [በዳንኤል 7 የተገለጠው ወደ ፍጻሜ ዘመን ሲሆን ላይኛ ስልጣን ከሆኑት አገራት አራተኛው ነው።] አንተ፡ አራተኛውም፡ መጥተህ፡ ያለፉትን፡ እለዚያን፡ እንስሳ፡ ሁሉ፡ ድል፡ አድርጋችኋል። በብዙ፡ ድካም፡ በብዙ፡ ሕማም፡ ይህንም፡ ዓለም፡ ቀምተሃል። ይህን፡ ያህል፡ ዘመን፡ በዚህ፡ ዓለም፡ በተንኰል፡ ኖረህ፡ ይችን፡ ዓለም፡ በጽኑ፡ አገዛዝ፡ ገዝተሃል። ዓለሙንም፡ ፈርደህ፡ በእውነት፡ አልነበረም። ጻድቃንን፡ ቀምተሃቸዋልና፡ ደጋጎቹ፡ ሰዎችንም፡ በድለሃቸዋልና፡ ቅኖቹንም፡ ጠልተህ፡ አሰተኞቹን፡ ወደሃቸዋልና፡ የጻድቃንን፡ አምባቸውን፡ አፍርሰሃልና፡ ያልበደሉትን፡ ሰዎች፡ ቅጽራቸውን፡ አፍርሰሃልና። ኃጢአትህም፡ ወደ፡ እግዚአብሔር፡ ደርሳለችና፡ ትቢትህም፡ ወደ፡ ኃያል፡ እግዚአብሔር፡ ደርሷልና። እግዚአብሔርም፡ ወገኖቹ፡ በቸርነቱ፡ ተመልክታችኋልና፡ መከራ፡ የሚቀበሉት፡ ዘመን፡ እነሆ፡ ተፈጽሟልና። ስለዚህ፡ ነገር፡ አንተ፡ ንሥር፡ ትጠፋለህ። ኃጢአተኞች፡ ታናናሽ፡ ክንፎችህ፡ ወገኖችህ፡ የእግዚአብሔርን፡ ሕግ፡ የዘነጉ፡ ጥቃቅን፡ ነገሥታቶችህም፡ ክፉዎች፡ የሆኑ፡ ሠራዊቶችህም፡ ይጠፋሉ። ምድርም፡ ከመከራዋ፡ ሁሉ፡ እፎይ፡ ብላ፡ ካንተ፡ ጭቆና፡ ታርፍ፡ ዘንድ፡ የፈጣሪዋን፡ ቸርነቱንና፡ ፍርዱን፡ ተስፋ፡ ያደርግ፡ ዘንድ፡ በደለኞች፡ ሰውነትህም፡ ይጠፋል።»

ከዚህ፡ በኋላ፡ ፈጣሪ፡ እግዚአብሔር፡ ለዚያ፡ ላሞራ፡ ይህን፡ ቃል፡ በነገረው፡ የቀረው፡ ይህ፡ ራስ፡ ጠፋ፡ [የቀረው ዘርፍ፡ ጠፋ]። ወደሱ፡ የመጡ፡ እነዚያም፡ ክንፎች፡ ተነሡ። እሊህም፡ ይገዙ፡ ዘንድ፡ ተነሡ፡ [ወደዚያ ዘርፍ ሔደው የነበሩት መጨረሻ ሁለት ደካም ወራሾች አሁን ግዛታቸውን ያጽናሉ]። በጥፍራቸውም፡ (ሠራዊት፡) ታወኩ።

ከዚህ፡ በኋላ፡ እነሱም፡ ጠፉ። የንስርም፡ ሥጋ፡ ሁሉ፡ ተቃጠለ። ምድርም፡ ፈጽማ፡ ደነገጠች።

[...]

«ያየኸው፡ የዚህ፡ የሕልምህ፡ ትርጓሜ፡ እንዲህ፡ ነው፡» አለኝ። «ከባሕር፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አሞራ፡ ለወንድምህ፡ ለዳንኤል፡ በሕልም፡ የታየችው፡ አራተኛዋ፡ መንግሥት፡ ናት። [በዳንኤል ምዕ. 7] ዛሬ፡ ላንተ፡ እኔ፡ እንደተረጐምኩልህ፡ ነገር፡ ግን፡ ለሱ፡ አልተረጐምሁለትም።

እነሆ፡ ዘመን፡ ይመጣል። በዚህ፡ ዓለምም፡ ከሷ፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ መንግሥታት፡ ይልቅ፡ የምታስፈራ፡ መንግሥት፡ ትነሣለች። በሷም፡ አሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ ይነሣሉ። ዳግመኛ፡ የሚነግሠውም፡ ካሥራ፡ ሁለት፡ ነገሥታት፡ በዘመኑ፡ ፈጽሞ፡ የሚበልጥ፡ ነው። ያየሃቸው፡ የሊህ፡ ያሥራ፡ ሁለቱ፡ ክንፎች፡ ትርጓሜ፡ ይህ፡ ነው። ቃልን፡ ከሰውነቱ፡ መካከል፡ እንጂ፡ ከራሶቹ፡ ሳይሆን፡ ሲናገር፡ ያየኸው፡ ይህም፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው። ከዚያም፡ መንግሥት፡ ታላቅ፡ ትግሎች፡ ይነሣሉ። መንግሥት፡ እጠፋ፡ እጠፋ፡ ትላለች። በግዛቷ፡ እጅግ፡ ጸንታ፡ ትኖራለች፡ እንጂ፡ ነገር፡ ግን፡ ያን፡ ጊዜ፡ አትጠፋም። ከክንፎቹ፡ ስምንት ታናናሽ ክንፎች፡ ሲወጡ፡ ያየኸውም፡ ይህ፤ ትርጓሜው፡ እንደዚህ፡ ነው። ዘመናቸው፡ የከፋ፡ ወራታቸው፡ ያጠረ፡ ፰፡ ነገሥታት፡ በሷ፡ ይነግሣሉ። ሁለቱ፡ ግን፡ ከነሳቸው፡ በዘመናቸው፡ መካከል፡ ፈጥነው፡ ይጠፋሉ። ነገር፡ ግን፡ ዓራቱ፡ ፍጻሜው፡ ዘመን፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ይጠበቃሉ፡፡ ሁለቱም፡ [ዙፋኑን አልፈው ወደ ሦስተኛው ዘርፍ የሚሔዱት መጨረሻ 2 ደካም ወራሾች] ለፍጻሜው፡ ዘመን፡ ይጠበቃሉ። ዝም፡ ብለው፡ ያየሀቸው፡ እነዚህም፡ ሦስቱ፡ ራሶች፤ ትርጓሜው፡ እንዲህ፡ ነው። እግዚአብሔር፡ ብኋላ፡ ዘመን፡ ሦስቱን፡ ነገሥታት፡ ያስነሣል። በውስጧም፡ እንግዳ፡ ነገር፡ ይሠራሉ፡ ምድርንም፡ መከራ፡ ነገር፡ ያጸኑባታል። ከሳቸው፡ አስቀድሞ፡ ከነበሩት፡ ከነገሥታቱ፡ ሁሉ፡ ይልቅ፡ በውስጧ፡ የሚኖሩትንም፡ ስዎች፡ በብዙ፡ ፍራት፡ መከራ፡ ያጸኑባቸዋል። የመንግሥት፡ መገኛ፡ ናቸውና፡ ስለዚህ፡ ነገር፡ ከነገሥታት፡ በላይ፡ ተባሉ፡ [ሦስቱ የመንግሥት ዘርፎችና በመጨረሻ ብሔራዊ ጦርነት ውስጥ መሪዎቻቸው ናቸው]። ታላቅ፡ ራሱ፡ ሲጠፋ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ በመኝታው፡ የሚሞት፡ ከለሳቸው፡ አንዱ፡ ነው፡ ነገር፡ ግን፡ ተጨንቆ፡ ይሞታል፡ [«ፊተ ጨካኝ ንጉሥ»]። የቀሩት፡ ሁለቱ፡ ግን፡ በጦር፡ ይሞታሉ። አንዱ፡ ባልንጀራውን፡ በጦር፡ ያጠፋልና፡ ነገር፡ ግን፡ እሱ፡ ደግሞ፡ ኋላ፡ በጦር፡ ይሞታል፡ [በቀኝ ዘርፍና በግራ ዘርፍ መካከል ያለው ብሔራዊ ጦርነት]። በየማናዊ፡ ሥልጣን፡ የጸኑ፡ በቀኝ፡ በኩል፡ ወዳለው፡ ራስ፡ ሲሔዱ፡ ያየሀቸው፡ እሊህስ፡ ሁለቱ፡ ታናናሽ፡ ክንፎች፡ [መጨረሻ ሁለቱ ደካም ወራሾች]፤ ትርጓሜው፡ ይህ፡ ነው። እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቃቸው፡ የጥፋት፡ መጀመሪያ፡ የሚደረግባቸው፡ ናቸው። አንተ፡ እንዳየኸውም፡ ብዙ፡ ጸብ፡ ክርክር፡ ይደረጋል።

ከምድረ፡ በዳ፡ እያናፋ፡ ሲወጣ፡ ያየኸው፡ ይህ፡ አንበሳ፡ ያን፡ አሞራ፡ የተናገረው፡ በኃጢአቱም፡ የሰደበው፡ የሰማህ፡ ይህ፡ ሁሉ፡ ነገር፤ እግዚአብሔር፡ ለኋላ፡ ዘመን፡ የጠበቀው፡ ከዳዊትም፡ ወገን፡ የሚወለድ፡ መሢህ ነው [እያንዳንዱም ጊዜ ከደቂቀ፡ ሰሎሞን፡ ይወለዳል]። መጥቶም፡ ኃጢአታቸውን፡ ይነግራቸዋል። ስለበደላቸውም፡ ይሰድባቸዋል። በፊታችውም፡ ፍዳቸውን፡ ይገልጥባቸዋል። በደኅነኛቸው፡ አስቀድሞ፡ ያቆማቸዋል። ከሰደባቸውም፡ በኋላ፡ ያን፡ ጊዜ፡ ያጠፋቸዋል። የቀሩ፡ ወገኖች፡ ግን፡ በቸርነቱ፡ በከበረ፡ አውራጃየ፡ ኢየሩሳሌም፡ ያድናቸዋል። አስቀድሜ፡ የነገርኩህ፡ ዕለተ፡ ምጽአትም፡ እስኪደርስ፡ ድረስ፡ ደስ፡ ያሰኛቸዋል። ...