FANDOM


መልአከ ደስታ ሆይ፥ በምደር ላይ ወርደሽ፥ ለምድራዊት እማማና ለሰማዩ አባት ልጆች ሁሉ ቁንጅናንም ፍሥሐንም አፍሰሺላቸው!

መልአከ፡ ደስታEdit

፩፤ ስድስተኛው ቁርባን ከመልአከ ደስታ ጋር ነው፤
ለሰው ልጆች ሁሉ ቁንጅናን ታሳድር ዘንድ በምድር ላይ የምትወርደው እርስዋ ናት።
፪፤ እግዚአብሔር፡ በኅዘን፡ ወይም፡ በልቅሶ፡ አይመሰገንምና፡
ሰቆቃዋችሁንና፡ ወዮታችሁን፡ ለቅቃችሁ፡
ለእግዚአብሔር፡ አዲስ፡ ምስጋናን፡ አመስግኑ፤
ምድር፡ ሁሉ፡ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር፡ እልል፡ በሉ።
፫፤ ሰማያት፡ ደስ፡ ይበላቸው፤ ምድርም፡ ሔሤት፡ ታድርግ፤
ሜዳው፡ ደስ፡ ይበለው፤ ወንዞችም፡ በእጅ፡ ያጨብጭቡ፤
ተራሮች፡ በእግዚአብሔር፡ ፊት፡ በአንድነት፡ ደስ፡ ይበላቸው።
፬፤ እናንተም፡ በደስታ፡ ትወጣላችሁ፤
በሰላምም፡ ትሸኛላችሁ፤
ተራሮችና፡ ኮረብቶች፡ በፊታችሁ፡ እልልታ፡ ያደርጋሉ።
፭፤ መልአከ፡ ደስታ፥ የምድራዊት፡ እማማ፡ ቅድስት፡ መልዕክተኛ፡ ሆይ፥
በሕይወቴ፡ ሳለሁ፡ ለእግዚአብሔር፡ እቀኛለሁ፣
ለአምላኬም፡ በምኖርበት፡ ዘመን፡ ሁሉ፡ እዘምራለሁ። ሥላህ

መልአከ ደስታEdit

ሰማያት ይፈግጋሉ፣ ምድርም ትፈንጠዛለች፣
አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ይዘምራሉ፣
የብርሃንም ልጆች ሁሉ እልል ይላሉ። [1]

 • ለሰማዩ አባት አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤
  ምድር ሁሉ፣ ምድራዊት እማማን አመስግኑ። [2]
 • ሰማያት ደስ ይበላቸው፣ ምድርም ሐሤትን ታደርግ፤
  ባሕርና የመንግሥተ ሰማያት ሞላ ይናወጡ፤[3]
  በረሃ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ፤
  የዱር ዛፎች ሁሉ በዚያን ጊዜ በሕግ ቅዱስ ፊት ደስ ይላቸዋል።
 • ሰማየ ሰማያት ሁሉ፣
  የሰማያት በላይም ውኃ፤[4]
  ተራሮች ኰረብቶችም ሁሉ፣
  ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤
  የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ፣
  አራዊትም እንስሳትም ሁሉ፣
  ተንቀሳቃሾችም የሚበርሩ ወፎችም፤
  የምድር ነገሥታት አሕዛብም ሁሉ፣
  አለቆች የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤
  ለሰማዩ አባት አመስግኑ፤
  ጒልማሶችና ቈነጃጅቶች፣
  ሽማግሌዎችና ልጆች፤
  ለሰማዩ አባት በደስታ ያመስግኑ።[5]
 • ለእግዚአብሔር በመስንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።
 • በዋሽንትና በመለከት ድምፅ
  በመላእክት ፊት እልል በሉ።
 • ወንዞች በእጅ ያጨብጭቡ፤ [6]
  ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት በአንድነት ደስ ይበላቸው።
 • ምድር ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፣
  በሐሤትና በደስታ ለሰማዩ አባትና ለምድራዊት እማማ ተገዙ፣
  በመዝሙር ወደ ፊታቸው ግቡ። [7]
  *የሕግ ቅዱስ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣
  ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ፡
  ሽማግሌዎቹ ቀብተውኛልና፤
  ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣
  ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን፡
  እናገር ዘንድ ልከውኛልና።
 • የሚያለቅሱትንም ሁሉ እጽናና ዘንድ፣
  ቅዱስ መልአከ ደስታን እልካቸው ዘንድ፣
  በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣
  በኅዘንም መንፈስ ፋንታ የብርሃንን መጐናጸፊያ፡
  እሰጣቸው ዘንድ ልከውኛልና።[8]
 • ልቅሶ ማታ ይመጣል፣
  ጥዋት ግን ደስታ ይሆናልና።[9]
 • በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን ያያል፤
  በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ የሕግ ቅዱስ ብርሃን ይወጣላቸዋል።[10]
 • እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ፡
  ደመናትም ደስታን ያዝንቡ[11]
 • በቅዱስ በዓል እንዲካፈሉ፣
  በዘላለማዊ ባሕር ከሚቆመው ሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበሉም፣
  የኅዘን ሰዎች በደስታ ይውጡ በሰላምም ይሸኙ፤
  ተራሮችና ኮረብቶች በፊታቸው እልልታ ያድርጉ።[12]
 • ከዚያ በኋላ ሕጉ የዘላለም ብርሐናቸው፣
  የሰማዩ አባትና ምድራዊት እማማ የዘላለም ክብራቸው ይሆናሉና፡
  ፀሐይ በቀን ብርሃን አኡሆንላቸውም፣
  የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያበራላቸውም።
 • ሕጉ የዘላለም ብርሃናቸው ይሆናልና፣
  የልቅሶአቸውም ወራት ታልቃለችና፡[13]
  ፀሐያቸው ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃቸውም አይቋረጥም።
 • የብርሃንን ልብስ አልብሰውኛልና፣
  የደስታንም መጐናጸፊያ ደርበውልኛልና፡
  በሕግ ቅዱስ እጅግ ደስ ይለኛል፣
  ነፍሴም በመላእክት ሐሤት ታደርጋለች።
 • ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፣
  ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፣
  እንዲሁ የሰማዩ አባት ሕግ ቅዱስን በተድላም በደስታም፡
  በብርሃን ልጆች ሁሉ ፊት ያበቅላል። [14]
 • በወንድማማች ገነት ምድር ሁሉ በቅድስናና በብዙ ደስታ ታበራለች፣
  በዚያ የሕግ ቅዱስ ዘር ይዘራልና።
 • ሕግ ቅዱስ ለብርሃን ልጆች ከሁሉ ጠቃሚ ነው።
  ለነሱ ክብርም ሞገስም፣ ለነሱ የሰውነት ጤና፣ ለነሱ የሰውነት ጉልበት፣
  ለነሱ የመላዕክት ረጅም ሕይወትና ደስታ ለዘላለም ዓለም ይሆናል።[15]
 • በወንድማማች ገነት እየኖርን ለሰማዩ አባት ለምድራዊት እማማና ለመላእክቱ ሁሉ እንዘምራለን።
  ለዘላለም ዓለም ለሕግ ቅዱስ ምስጋናን እናመስግናለን። ሥላህ።


 1. ኢዮብ 38፡7
 2. መዝ. 95፡5
 3. መዝ. 95፡11-12
 4. መዝ. 148፡4
 5. መዝ. 148...
 6. መዝ. 97፡5-8
 7. መዝ. 99፡1-2
 8. ኢሳይያስ 61፡1-3
 9. መዝ. 69፡5
 10. ኢሳይያስ 50፡2
 11. ኢሳይያስ 45፡8
 12. ኢሳይያስ 45
 13. ኢሳይያስ 60፡19-20
 14. ኢሳይያስ 61፡
 15. ያሽት 1፡33