FANDOM


መልአከ መንግሥተ ሰማያትEdit

  1. የመንግሥተ ሰማያትን መልእክት ለሰው ልጆች ከሚያመጣው ከመልአከ መንግሥተ ሰማያት ጋራ አራተኛው ቁርባን ነው።
  2. ከመላእክት ጋራ የሚሔድ ከደመናት በላይ ለመምጠቅ ይማራልና፣ የሕይወት ቅዱስ ዛፍ በሚቆምበት በዘላለማዊው ባሕር ውስጥ መኖሪያው ይሆናል።
  3. ሞት ታላቅ ምስጢሩን እስኪገልፅ ድረስ አትቆይ። እግርህ በመሬቱ አፈር ላይ እየተራመደ የሰማዩን አባትህን ካላወቅክ፣ በዘመነ መንግሥተ ሰማያት ከጥላ በቀር ምንም አይኖርህም።
  4. እዚህም አሁንም ምስጢሩ ይገለፃል፤ እዚህም አሁንም መጋረጃው ይነሣል። አትፍራ፣ አንተ ሰው ልጅ ሆይ።
  5. የመልአከ መንግሥተ ሰማያትን ክንፍ ያዝ፤ የመንገድም ፍጻሜ ለመድረስ ዘወትር ወደ ዞሩት ወደ ከዋክብት፣ ወደ ጨረቃ፣ ወደ ፀሐይ፣ ወደማይቋረጥ ብርሃን ጎዳና ብረር፤ ወደ ሰማዩ ዘላለማዊ ሕይወትም ባሕር ምጠቅ። [በያሽት 13:57-58]

ሥላህ።