FANDOM


መልአከ ጸሐይEdit

መልአከ ፀሐይ ሆይ፥ ሰውነቴን ገብተሽ፥ በሕይወት እሳት ልታጠብ!መጀመርያው ቁርባን ከመልአከ ፀሐይ ጋር ነው።
ወርቃማ ብርሃንዋን በዓለም ታፍሰስ ዘንድ
ጧት ጧት እንደ ሙሽሪት ከእልፍኝዋ የምትወጣው[1] እርሷ ናት።
አንቺ ብሩህ መልአከ ፀሐይ ሆይ፥ ሕያው ክቡር ፈጣን ፈረስ![2]
ያላንቺ ሙቀት፥ እሳትም፥ ሕይወትም የለም።
የዛፎቹ ልምላሜ ያመሰግንሻል።
ስለ አንቺ ትንሹ የስንዴ ቅንጣት ወርቃማ ጎንዛላ የሣር ወንዝ ሆኖአል።
ስለ አንቺ በሰውነቴ መካከል ያለችው አበባ ትከፈታለች።
ስለዚህ እኔ ራሴን ከአንቺ ከቶ አልሠውርም።
መልአከ ፀሐይ፥ የምድራዊት እማማ ቅድሥት መልእክተኛ ሆይ፥
በውስጤ ወዳለው ቤተ መቅደስ ገብተሽ የሕይወት እሳት ስጪኝ! ሥላህ

መልአከ ፀሐይEdit

ግባ፣ ውጣ፣ አንተ ብሩሕ ፀሐይ፣
ሕያው ክቡር ፈጣን ፈረስ፣
ከተራሮችም በላይ!
ጸዳልን ለፍጥረት አስግኝ! [3]
መልአከ ፀሐይ ሆይ፣ አንተ የብርሃን ምንጭ ነህ፤
አንተም ጨለማውን ታሳድዳለህ። [4]
የአድማሱን በር ክፈት! [5]
  1. [መዝሙር 19፡5]
  2. [ወንዲዳድ፣ ፋርጋርድ 21፡5]
  3. [ወንዲዳድ፣ ፋርጋርድ 21፡5]
  4. [ቃላተ መውጣት በቀን (የግብፅ ሙታን መጽሐፍ) 85]
  5. [ቃላተ መውጣት በቀን (የግብፅ ሙታን መጽሐፍ) 15]